ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩ የትግራይ ፖለቲካዊ ፓርቲዎች ለሁሉም ፖለቲካ ሃይሎች ያካተተ (የታጠቁና ያልታጠቁ) ግዚያዊ መንግስት ምስረታ ማቋቋም የሚያስችል የፖለቲካ ሃይሎች ውይይት እንዲደረግ በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ይህ በትግራይ ደረጃ የሚደረግ ውይይት እንዲካሄድ በመመሪያ የተሾሙ አባላት በግልና በፓርቲዎች የጋራ መድረክ የተሳካ ውይይት እንዲካሄድ ሰፊ ጥረት አድርገናል፡፡በተጨማሪም ሃገርና ህዝብ የሚያድኑ የሚያሻግሩ የተሳኩ ውይይቶች የተለያዩ ህዝቦችና አካባቢዎችን በመጥቀስ ትግራይ ከገባችበት የህልውና አደጋ የምትወጣበት ሂደት ዙሪያ ውይይት እንዲካሄድ የቻልነውን ያህል ተንቀሳቅሰናል፡፡ ይሁን እንጂ ትግራይ አቃፊና ሃቀኛ የፖለቲካ ሃይሎች ውይይት በማካሄድ የምትድንበትን አማራጭ ቢሆንም ስልጣን በብቸኝነት ሃገር በማፍረስ የተሰማራ ሃይል ሂደቱን እንዳይሳካ መሰናክል ሆኗል፡፡

የህወሓት ቡድን የትግራይ ተወላጆች ተሰብስበን እንዳንወያይ፤ የትግራይ ጉዳይ በትግራይ ተወላጆች እንዳይወሰን፤ ወደ ትጥቅ ትግል የተሸጋገረ የትግራይ ፖለቲካ ወደ ሰላማዊና ህጋዊ ፖለቲካ ትግል እንዳይመለስ፤ የትግራይ ብሄራዊ ጥቅም እንዳይረጋገጥ የሚተጋ አቃፊ ግዚያዊ መንግስት እንዳይቋቋም ቸንክሮ በመያዝ በትግራይ የተፈጠረውን ሁለንተናው ቀውስ እንዲባባስ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህ ቡድን የትግራይ ፖለቲካዊ ምህዳር ትግራይ ለሰላማዊና ህጋዊ ትግል ዝግ በማድረግ ከአካባቢያዊ ሃይሎች በተለይም ከህግዴፍ (ሻዕብያ እና ፋኖ) ወታደራዊ ፅምዶ (ቅንጅት) በመፍጠር እያውደለደለ ይገኛል፡፡
እንደሚታወቀው ሻዕብያ ከተፈጠረ ጀምሮ ፀረ- ትግራይ ህልውና የቆመ ሃይል ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ የትግራይ ህልውና ለማጥፋት የተሰማራ ሃይል ተቀናጅቶ ሃገራችን ያወደመ በባለፈው ዘር ማጥፋት ዘመቻ ጦርነትም የእራሱን ድርሻ የተጫወተ፣ ህዝባችን የጨፈጨፈ ጨካኝ ሃይል ነው፡፡ ስለሆነም ለወንድማችን የኤርትራ ህዝብ እንደይዞታ (እንደርስት) ይዞ ለባርነት የዳረገ፣ ህዝባችን በዘር ማጥፋት ጦርነት የጨፈጨፈ ሃይል የሚደረግ ህገ- ወጥ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጥምረት ለትግራይ ዕዳ እንጂ ፀጋ (ምንዳ) አይደለም፡፡
በሌላ በኩል የህወሓት ቡድንና የፀጥታ ሃይል አባላት በግል በፖለቲካ የሚሳተፉ የትግራይ ተወላጆች እያፈኑ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ነባር የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ አመራር ብርጋዴል ጀነራል ጉዕሽ ገብረና በርካታ የትግራይ ፀጥታ ሃይል አመራርና አባላት እንዲሁም የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ባለፉት ቀናት ታፍኗል፡፡
እነዚህ ወገኖች እስከ አሁን ወደ ፍርድቤት አልቀረቡም፡፡ የሚገኙበት ቦታም አይታወቅም፡፡በመሆኑም አሁን ባለው ለውጦች ይህ የአፈና ተግባር ህገ- ወጥ ፅምዶ (ቅንጅት) የሚቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ በግል በማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች፤ የፀጥታ አካላት አመራርና አባላት እንዲሁም ሌሎች ይህንን የሚቃወሙ ወገኖች ሊቀጥል እንደሚችል መረዳት ችለናል፡፡
በመሆኑም፡-
1. በጀነራል ጉዕሽ ገብረና ሌሎች የትግራይ ፀጥታ ሃይል አባላት የተፈፀመ አፈና የታጠቁና ስቪል ታጋይ የትግራይ ተወላጆች በሰላማዊ ትግል ላይ የነበራቸው ጭላንጭል ተስፋ ተማጥጦ አማራጭ አጥተው ወደ ትጥቅ ትግል አማራጭ አድርገው የእርስ በእርስ ጦርነት ለመቀስቀስ በር የሚከፍት አደገኛ ተግባር ስለሆነ በጥብቅ እናወግዘዋለን፡፡
2. ከሻዕብያ ጋር የሚካሄደው ፅምዶ (ቅንጅት) የተባለ የሻዕብያ ጣልቃ ገብነት ትግራይ የጦርነትና የግርግር ማዕከል ለማድረግ የሚካሄድ አደገኛ እንቅስቃሴ ሊቆም ይገባል፡፡
3. በትግራይ ደረጃ የተጀመረ ውይይት በህወሓት ጣልቃ- ገብነትና በግዚያዊ አስተዳደር ተባባሪነት ተደናቅፏል፡፡ ይሁንና የተወሳሰበ የትግራይ ችግር አሁንም በአቃፊ ውይይት ይፈታል የሚል እምነት አለን፡፡ በመሆኑም ሁሉም ፖለቲካዊ ሃይሎች ትግራይ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በእኩልነት የሚሳተፉበት ውይይት እንዲካሄድ ሁሉም አካል ጫና ሊያሳድር ይገባል እንላለን፡፡
4. የህወሓት ቡድን በአካል ጉዳተኞች ስም፣ በተፋናቃይ ወገኖችና በሌሎች የህብረተሰብ ክፍል ከህዝባችን በግዳጅ ለመሰብሰብ ያቀደው 6 ቢሊዮን ብር በጦርነት የወደመ የትግራይ ኢኮኖሚ ሙሉ ለሙሉ ወገቡን የሚሰብር፤ በከበባና መዘጋት የተጎዳ ህዝባችን ወደ ከፋ መከራ የሚያስገባ፤ ይህ ለገዢዎች እጅ መንሻ ስለሆነ ሊቆም እንደሚገባና ህዝባችንም አንከፍልም በማለት ብሄራዊ እምቢተኝነት እንዲያካሂድ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህ በወገኖቻችን ስም እንዲሰበሰብ የታሰበው ገንዘብ ለአካል ጉዳተኞችና ተፈናቃዮች እንደማይውል
5. በተደጋጋሚ ስለታየ፤ የህወሓት ቡድንም የማይታመን መሆኑ ስለተረጋገጠ ይህ ቡድን የሚያካሂደው ማንኛውም ዓይነት ገንዘብ ማሰባሰብ ቅቡልነት የለውም፡፡
እኛ 6 የፖለቲካ ፓርቲ ተከታታይናቀጣይነት ያለው ትግል ስለምናካሂድ ህዝባችን በቀጣይ በምንገልፀው ፖለቲካዊ ትግል ህዝባችን ከጎናችን ተሰልፎ እንዲታገል ጥሪ እናቀርባለን፡፡
- ብሄራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና)
- ውድብ ነጻነት ትግራይ (ነፃነት)
- ዓረና ትግራይ ለነፃነትና ላዕላዊነት
- ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)
- ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ (ትሰእፓ)
- ውድብ ወለዶ ትግራይ(ወለዶ)












