
7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ግንቦት 24 እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ።
በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅትና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው ቦርዱ ግንቦት 24 የድምፅ መስጫ ቀን መሆኑን ይፋ አድርጓል ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ2018 7ተኛ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ለማከናወን አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየሰራ መሆኑን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሀይሉ ገልጸዋል ።
የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች እና እጩዎች ምዝገባ በዲጂታል እና በማንዋል እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን በዲጂታል ለማድረግ የሚያስችል ሶፍትዌር መበልጸጉ ተመላክቷል።
በ – ሰላማዊት ወልደገሪማ
Source:
NBC Ethiopia
Via:
NBC Ethiopia












