
የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ለፍትህ ፣ ለነጻነት ፣ለዲሞክራሲ እና ለህገመንግስት መከበር ትልቅ መሰረት የሚጥል መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር ገለጹ።
20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በቡሌ ሆራ ከተማ ተከብሮ ውሏል።
እለቱ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በህላቸውን፣ ቱፊታቸውን እና እሴታችን እንዲያስተዋውቁ የሚረዳ ነው ተብሏል።
በተጨማሪም የብሔር ብሔረሰቦች ትውውቅን እና አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑ ተመላክቷል።

የዘንድሮውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ታላቁ የህዳሴ ግድብ እውን የሆነበት እና የተፈጥሮ ጋዝን ጨምሮ ሌሎች ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የተጀመረበት በመሆኑ ልዩ ያደርዋል ነው የተባለው።
በበዓሉ ላይ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘው ተሻገርን ፣የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረማንን ጨምሮ ከተለያዩ ክልሎች ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች ፣አባ ገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎችን ፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ ከተሞች የተውጣጡ ብሔር ብሔረሰቦች ተገኝተዋል።
የአብስራ ብርሃኑ












