NBC Ethiopia
December 1, 2025
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዘንድሮ የሀጅ ጉዞ ምዝገባን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የዘንድሮ የሀጅ ጉዞ ምዝገባ ዋጋ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በዶላር የ15 ነጥብ 6 በመቶ በመቀነስ ከነበረበት 4ሺህ 921 ዶላር ወደ 4 ሺህ 228 ዶላር እንዲሆን መወሰኑን አመልክቷል። ሆኖም የብር የመግዛት አቅም ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ልዩነት ያሳየ በመሆኑ የሀጅ አገልግሎትና መስተንግዶ ዋጋ 7 መቶ 40 ሺህ ብር ሊሆን መቻሉ ነው የተገለፀው።

የ2018 የሀጅ ጉዞ ምዝገባ ማድረግ የሚፈልጉ ተጓዦች በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የምዝገባ ጣቢያዎች ቀርበው መመዝገብ እንደሚችሉ የተጠቆመ ሲሆን ምዝገባው የሚቆየው እስከ ጥር 26/2018 ድረስ ብቻ መሆኑም ተገልጿል። ከባድ የጤና እክል ያለበት ሰው የህክምና ባለሙያዎችን ሳያማክር መጓዝ እንደማይችል ተጠቁሟል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












