Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ማርቆስ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ማርቆስ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

December 2, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

December 2, 2025

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደብረ ማርቆስ እየተገነባ የሚገኘውን ዘመናዊ ሆስፒታል፣ የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) እያስገነባው የሚገኘውን ሕንጻ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ የከተማዋን እድገት እና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውን ገልጸው፣ በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ባለቤትነት እየተገነባ የሚገኘው ሆስፒታል በመጠናቀቅ ላይ መኾኑን አስታውቀዋል። ሆስፒታሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አልጋዎች ያሉት፣ ለደብረ ማርቆስ እና አካባቢው ሕዝብ ሰፊ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብለዋል። በሽታን ለመከላከል እና አክሞ ለማዳን በሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አንስተዋል።

ሆስፒታሉ ለከተማዋ ተጨማሪ አቅም እንደሚኾንም ገልጸዋል። እስከ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደኾነም ተናግረዋል። ሆስፒታሉ በሌላ ተቋራጭ ይሠራ እንደነበር እና ረጅም ጊዜ መውሰዱን ያስታወሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው፣ የመንቆረር ኮንስትራክሽን ከተረከበው በኋላ ግን በፍጥነት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ባለቤትነት እየተገነባ የሚገኘው ሕንጻም በመጠናቀቅ ላይ መኾኑን ተናግረዋል። በፍጥነት እየተሠራ የሚገኘው ግንባታው ባሕላዊ እና ታሪካዊ ይዘቶችን እንደያዘም ገልጸዋል። ግንባታው በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቅም ተናግረዋል። በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውንም አስታውቀዋል። በከተማዋ የተፈጠረው አንጻራዊ ሰላም የልማት ሥራዎችን ለመሥራት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ተናግረዋል።

ማኅበረሰቡ ሰላሙን እየጠበቀ ወደ ልማቱ እየዞረ ነው ያሉት አቶ ተሾመ ዋለ፣ በዚህ ዓመት ከማኅበረሰቡ ጋር በመኾን በርካታ የልማት ሥራዎችን ለመሥራት አቅደናል ነው ያሉት። የተጀመሩ ይጠናቀቃሉ፤ ሌሎች አዳዲስ የልማት ሥራዎችም ይሠራሉም ብለዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና ሌሎች ሥራዎች ትኩረት እንደሚደረግባቸውም ተናግረዋል። የከተማዋን ገቢ የመሰብሰብ አቅም ለማሳደግ እየተሠራ መኾኑንም አስታውቀዋል። የሕዝብን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ ሥራዎች እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

ከተማዋ ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋች ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የሕዝብን ጥያቄ መሠረት ያደረጉ እና የከተማዋን እድገት የሚመጥኑ የልማት ሥራዎች ይሠራሉ ነው ያሉት። በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳደሩን ጨምሮ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: EthiopiaFacebookhospitalMeta
ShareTweetShare
Previous Post

የህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የምሽት ዜናዎች

Next Post

የህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የቀን ዜናዎች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የቀን ዜናዎች

የህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም የኤንቢሲ ኢትዮጵያ የቀን ዜናዎች

በምስራቅ አፍሪካ ትልቁን የካፒታል ገበያ የመፍጠር ጉዞ

በምስራቅ አፍሪካ ትልቁን የካፒታል ገበያ የመፍጠር ጉዞ

ተግባራዊ ማሻሻያዎች የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ጨምረዋል

ተግባራዊ ማሻሻያዎች የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ጨምረዋል

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?