Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ከዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

ከዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

November 7, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

ፓርቲያችን ስምረት ትግራይ ከገባችበት ሁለገብ ቀውስ እንድትወጣ በትግራይ ያሉ የፖለቲካ ልዩነቶች ሁሉንም ትግራዋይ ባሳተፈ ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ በውይይትና የትግራይን አንድነት በሚያጠናክር መንገድ እንዲፈቱ ብሎም ትግራይ ወደ መልሶ ግንባታ እንድትገባ በተደጋጋሚ ጥሪ ስናቀርብ ቆይተናል።

ይሁን እንጂ ትግራይን እንደ ግል ንብረቱ አድርጎ የሚያስብው ኃላ ቀር ቡድን እና በስሩ ያሉ ጠባቂዎቹ ሁሉን ዓይነት አማራጮች በመዝጋት “እኔ በምለው ትሄዳላችሁ” በማለት ትግራይን ወደከፋ አዘቅት እየጣሏት ይገኛሉ።

ካለፈው ስህተታቸው ያልተማሩት እነዚህ የጥፋት ቡድኖች አሁን ድግሞ መውጫ መንገድ ብለው የያዙት ህዝባችንን ከጨፈጨፈው፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን፣ ጎልማሶች እና እናቶችን በአጠቃላይ በትግራይ ሴቶች ላይ አስከፊ ግፍ ከፈጸመው፣ ቤተ እምነቶቻችንን ካረከሰው፣ ከፋብሪካ እስከ ማንኪያ፣ ከጀሪካን እስከ መኪና የዘረፈውን… በአጭሩ በትግራይ ታሪክ ህዝብ ይቅር የማይለው ግፍ ከፈጸመው ሻዕቢያ ጋር “ፅምዶ” የሚል ጥምረት በመመስረት ጦርነት አውጇል።

በጌታው የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሲቪል ማኅበረሰብ ጥሪ እንዳልሰማ በመሆን በአዲ ወጀራት እና ራያ ዓዘቦ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው የትግራይ የሰላም ኃይል ላይ ጥቃት ሰንዝሯል፡፡

እንዲሁም በወጣት ትግራዋይ ወንድሞቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት ሳይጸጸት ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የፕሪቶሪያን ስምምነት በመጣስ ግልጽ ጦርነት በማስነሳት 6 የአፋር ቀበሌዎችን ተቆጣጥሮ ይገኛል።

ይህ እርምጃ የፕሪቶሪያን ውል ብቻ የሚጥስ ሳይሆን ሕገ መንግሥትን፣ ክልላዊ ወሰኖችንና እሴቶችን የሚጥስ ነው፡፡ ከአፋር ሕዝብ ጋር መልሰን የጀመርናቸውን ጠንካራ ግንኙነቶች የሚያፈርስ እና ሕዝባችንን ለሌላ አደጋ የሚያጋልጥ ነው።

ይህ አጥፍቶ ጠፊ እና ተስፋ የቆረጡ ሰዎች የወሰኑት ውሳኔም ነው። ቡድኑ ይህ ጦርነት የጀመረበት ያለው ዋና ምክንያት በአንድ በኩል ይህ ወደ ኋላ የቀረው ቡድን በሕዝቡ የገጠመው ተቀባይነት ማጣት እንዲሁም እንደ መጫወቻ ካርድ ሲጠቀምባቸው የቆዩት ተፈናቃዮችን መመለስና የትግራይን ሕገ መንግሥታዊ ወሰን ማስጠበቅ የሚሉትን አጀንዳዎች እንዲተዉና እንዳይተገበሩ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

በሌላ በኩል በፌዴራል መንግሥትና በህግደፍ ስርዓት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት በመጠቀም ሻዕቢያ የማይቀር ነው ብሎ የገመተውን ጦርነት ራቅ አድርጎ ለማስቀረት አገልጋዮቹ በደቡብ ትግራይና በአፋር እንዲዋጉ በሰጣቸው መመሪያ ነው።

ይህ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት የተነሳ “ትግራይን የማጥፋት ህልሜ ተቀጨ” ብሎ ከተቆጨውና አሁንም “አልጸጸትም” ከሚለው ሻዕቢያ እና “ኤርትራ የሰረቅኩትን ይዤ መውጫዬ ትሆናኛለች” ብሎ ከሚያምነው ኋላቀር ቡድንና ከጠባቂዎቹ በስተቀር ለሌላ ትግራዋይ ሁሉ የጥፋት መንገድ ነው።

ለዚህም ነው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ይህንን ጦርነት ለማስቆምና የትግራይን ችግር በውይይት ብቻ ለመፍታት የሚታገለው! የተከበርከው የትግራይ ህዝብ! ይህ ኋላቀር አስተሳሰብ ያለውንና ጦርነት ናፋቂው ቡድን የውጭ ኃይሎች መሣሪያ ሆኖ የሚሰራ ቅጥረኛና ከዳተኛ ነው።

ከዚህ ቀደም ከፈጸማቸው ክፉ ተግባራት የማይማረው ይህ አሳፋሪ ቡድን፤ እየመራህ ሁሉንም ዓይነት መስዋዕትነት ብትከፍልም የምታስመዘግበው ድልና ዕድገት እንደሌለ በተደጋጋሚ ያረጋገጥከው እውነት ነው። አሁንም ቢሆን የሻዕቢያን ተልዕኮ ለመፈጸም ሲል ትግራይን የጦርነት ማዕከል እያደረጋት ስለሆነ መላው ሕዝባችን በብርቱ እንድትቃወም እና ልጆችህን ከተጨማሪ ጥፋት እንድታድን ስምረት ጥሪውን ያቀርባል።

የተከበርክ የትግራይ ሠራዊት! ለአንድ ወደ ኋላ ለቀረ ቡድንና “ከእኛ በላይ ኮር” ብለው በራስህ ላይ ለተቀመጡ ሰዎች ብለህ ሳይሆን ለአገርህና ለትግራይ ሕዝብ ብለህ ነው ከዚህ ቀደም ሁሉንም ዓይነት መስዋዕትነት የከፈልከው። ይሁን እንጂ በጥፋት ቡድኑ ጠባቂዎች ምክንያት ባለፈው በሰላማዊ ሰልፎችህ እንደገለጽከው ለዚያ ኋላ ቀር ቡድን መገልገያ እንድትሆን እና ኩራትህ የሆነው ሕዝብህ በጥርጣሬ እንዲያይህ አድርገውሃል።

አሁን ደግሞ በማይመለከትህ አጀንዳ ውስጥ ለራሳቸው ደኅንነት እና ሻዕቢያን ለመከላከል እያዘጋጁህ ነው። ከሰላም ኃይሎች ጋር ወይም ከማንኛውም አካል ጋር መዋጋት ተገቢ ስላልሆነ በሻዕቢያ በሚመራ ኮማንድ ሥር ሆነን አንዋጋም” እምቢ! እንድትል ስምረት ድርጅት ይጣራል።

የተከበርክ የትግራይ ህዝብና የትግራይ ወዳጆች እንዲሁም በውጭ የምትኖሩ ዲያስፖራዎች! የትግራይ ሕዝብ በፊት ወደ ነበረበት አስከፊ ከበባ እንዲሁም ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላም ቢሆን የነበረው ዘር ማጥፋት እንዲቀጥል ልንፈቅድ አይገባንም። ሕዝባችን ተርቧል እንጂ፣ የኋላ ቀር ቡድኑና ጠባቂዎቹ በወርቅና በጨርቅ ዝርፊያ ተጠምደው “ምንም አይጎዳችሁም፤ የትግራዋይን ነው የወሰድነው” እያሉ እየጮሁ እንደሚኖሩ የታወቀ ነው።

ስለሆነም ከሕዝባችን ጋር በመሆን እድሜ ልካቸውን ደም መጥጠው የማይጠግቡትን ለማስወገድ እጅ ለእጅ ተያይዘን ትግላችንን እንድናፋጥን ስምረት ጥሪ ያቀርባል። ክቡራን የትግራይ ፓርቲዎች እና ለውጥ ፈላጊዎች!

የእኛ ድርጅት ስምረት ትግራውያን በሀገራቸው ጉዳይላይ በውይይትና በእኩልነት የሚወስኑበትና የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታን መፍጠር መዘግየት የሌለበት ጉዳይ ነው ብሎ ያምናል። ልዩነቶቻች ከትግራይ ሕልውና በታች መሆናቸውን አምነን ትግራይ ላይያንዣበበውን አደጋ አንድ ሆነን ልንጋፈጠው ይገባል።ይህ ተስፋ የሌለው ቡድን ወደ እርስ በርስ ጦርነት ጎትቶ ወደ ከፋ ጥፋት ከማስገባቱ በፊት ሁላችንም የለውጥ ኃይሎች ተደራጅተንና ተቀናጅተን ልንመክተውእንደሚገባ ስምረት ድርጅት ይጣራል።

በመጨረሻም ያሉብንን ልዩነቶች በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ እንዲፈታ፣ በትግራይ ላይ ያንዣበበውንና የውጭ ተልዕኮ ያለው ጦርነት ለማስቆም ብሎም ይህንን ወደ ኋላ የቀረውን ተላላኪ ቡድን አስወግደን የጋራ የሆነች ዲሞክራሲያዊት ትግራይን ለመገንባት የተደራጀ ትግላችንን እንድናጠናክር እንጣራለን!

ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕታቶቻችን!

ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት)

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: EthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ኦፓሜካኖ ወደ ማድሪድ

Next Post

ድርቅ በኢራን

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ድርቅ በኢራን

ድርቅ በኢራን

“እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም”ሩሲያ

"እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም"ሩሲያ

የህዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም የቀን ዜናዎች | NBC ዜና | ቀጥታ ሥርጭት |

የህዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም የቀን ዜናዎች | NBC ዜና | ቀጥታ ሥርጭት |

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?