ሪያል ማድሪድ ዳዮት ኦፓሜካኖን ለማስፈረም በቃል ደረጃ መስማማቱ ተዘገበ።
ማድሪድ በውድድር አመቱ መጨረሻ የባየር ሙኒኩን ተከላካይ በነጻ ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር በቃ ደረጃ መስማማቱ ተነግሯል። የጀርመን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ኦፓሜካኖ በያዝነው የውድድር አመት መጨረሻ ውሉን በባየርን የሚጨርስ ሲሆን፤ ወደ ማድሪድ በነጻ ለመጓዝ መወሰኑ ተገልጿል።
ባየርን ሙኒክ ተጫዋቹን በክለቡ ለማቆየት የተሻሻለ ውል ቢያቀርብለትም፤ እየተደርገ ያለው ውይይት ውጤት አለማስገኘቱ ታውቋል። በየአመቱ ተጫዋቾችን በነጻ ማስፈረም ፋሽን ያደረገው ማድሪድ በቀጣዩ ክረምት የ27 አመቱን ኦፓሜካኖ የግሉ እንደሚያደርግ ተማምኗል ተብሏል።
ሪያል ማድሪድ ከኦፓሜካኖ በተጨማሪ በአውሮፓውያኑ 2027 በሊቨርፑል ውሉን የሚጨርሰውን ኢብራሆም ኮናቴንም በነጻ ለማስኮብለብ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












