ኢራን ያልተጠበቀ ድርቅ እንዳጋጠማት ተገለፀ።
በተለይም ዋና ከተማዋ ቴህራን ከባድ የውሃ እጥረት እንደገጠማት ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን አሳውቀዋል። ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዝቅተኛ የዝናብ መጠን በአገሪቱ ሲመዘገብ፤ የውሃ ማከማቻዎች ሳይቀሩ ባዶ ወደ መሆን ተሸጋግረዋል።
በቅርቡ ዝናብ የማይኖር ከሆነ የውሃ አጠቃቀም ገደብ ሊኖር እንደሚችልም ፕሬዚዳንቱ አሳስበዋል። የተፈጠረውን ቀውስ ለመቆጣጠርም በዚህ መንገድ ብቻ መንቀሳቀስ በቂ ላይሆን ይችላል ተብሏል።
ከዋና ከተማዋ ቴህራን ህዝቡንና አስተዳደሩን የማስወጣት ሀሳብ እንዳላቸውም ማሱድ ፔዜሽኪያን አስገንዝበዋል። ታሪካዊቷን ቴህራንን ወደ ሌላ ከተማ የመለወጥ አዝማሚያ ነው በሚልም እየተተቹ ነው።
በቴህራን ጋዜጦች እና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እየተተቹ የሚገኙት ቶሬዚዳንቱ አደጋው እንዳይከጋ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። የቀድሞ የቴህራን ከንቲባ ሳይቀሩ ቀልድ ነው በሚል የፔዜሽኪያንን ሀሳብ አጣጥለውታል።
ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ዝናብ ሊዘንብ እንደማይችልም ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።
ዘገባው የቢ ቢ ሲ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












