ፊዮረንቲና ሮቤርቶ ማንቺኒን ለመቅጠር ውይይት ላይ ነው ተባለ።
የጣሊያኑ ክለብ ፊዮረንቲና ደካማ የውድድር አመት እያሳለፈ በመሆኑ አሰልጣኝ ስታፋኖ ፒዮሊን ትላንት ማሰናበቱ ይታወሳል። ክለቡ ተተኪ የሚሆን አሰልጣኝ በማፈላለግ ላይ ሲሆን፣ሮቤርቶ ማንቺኒን በማናገር ላይ እንደሚገኝ ተዘግቧል።
ሮቤርቶ ማንቺኒ በተጫዋችነት ዘመናቸው ለፊዮተንቲና በመጫወት እና በአሰልኝነትም የመጀመሪያ ሃላፊነታቸው ክለቡን በአውሮፓውያኑ ሚሊኒየም የኮፓ ኢጣሊያ ዋንጫ እንዲያሸንፍ አስችለውታል።
ከዚያም በኋላ በተለይም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንችስተር ሲቲን እያሰለጠኑ በታሪካዊ መንገድ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፋቸው አይዘነጋም። ማንቺኒ ለመጨረሻ ጊዜ በነበራቸው ሃላፊነት የሳኡዲ አረቢያን ብሔራዊ ቡድን ማሰልጠናቸው ይታወሳል።
አሰልጣኙ ወደ ሃላፊነት መመልስ ይፈልጋሉ መባሉን ተከትሎ የቀድሞ ክለባቸውን ስራ ሊቀበሉ ይችላሉ ተብሏል። 10ኛ ሳምንት በደረሰው የጣሊያን ሴሪ ኤ ፊዮረንቲና 4 ነጥብ በመያዝ 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












