በጅማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 27ኛው አመታዊ የጤናው ዘርፍ ጉባዔ በኦሮሚያ ክልል የጤና ተቋማትን ለማስፋፋት ወሳኝ ተግባራት ሲከናወኑ መቆታቸውን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የኦሮሚያ ክልል የከተማ ክላስተር አስተባባሪ መስፍን መላኩ ተናግረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ለጤና አገልግሎት ወሳኝ የሆኑ ግብአቶች ለማሟላት የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል።
የጤና ስርዓትን ለማሻሻል የጤና ባለሙያዎች መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ያነሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በጤናው ዘርፍ ለሚሰማሩ የግል አልሚዎች የክልሉ መንግስት የተለያዩ ማበረታቻዎች ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ፕ/ር ነፃነት ወርቅነህ በበኩላቸው በሆስፒታሎች የስፔሻሊቲ አገልግሎቶች እየተስፋፉ፣ የመድሃኒት አቅርቦት እየጨመረ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
በመድረኩ የህይወት ዘመን የላቀ ሙያ አገልግሎት ዘርፍ ለሰባት ምሁራን እውቅና ተሰጥቷል።
በ – አክረም ኑርያ












