በህውኃት ሳቢያ በትግራይ የምስረታ ጉባኤውንማካሄድ ባለመቻሉ በአዲስ አበባ ለማድረግ መገደዱን የዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ አስታወቀ።
በምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲነት በተሰረዘው በህውኃት በትግራይ ክልል የተፈጠረውን የፖለቲካ ምህዳር መበላሸትን ለማስተካከል ብሎም የትግራይ ህዝብን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታትእንደሚሰራ የፓርቲው ግዜያዊ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አስታውቀዋል።
ፓርቲው በዛሬው ዕለት በሚያደርገው ጉባኤው አመራሮችን እንደሚመርጥ ብሎም ማኒፌስቶውን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
የዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ ድርጅት ሃላፊ ብርሃነ ገብረኢየሱስ በምርጫቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ አግኝቶ በመንቀሳቀስ በአጭር ግዜ 5 ሺህ 600 አባላትን መመዝገብ ቢችልም በሃይል በሚያምነው በህውኃት አካሄድ የፓርቲው ቢሮዎች መሰበራቸውን፣ አባላቱ መንገላታታቸውን አመላክተዋል።
ፓርቲው ለትግራይ ህዝብ የተሻለ የፖለቲካ ምህዳርን ለማምጣት የመታገያ ፓርቲ ለመሆንእንደሚሰራ ተጠቁሟል። የፕሪቶርያየሰላም ስምምነት ተፈጻሚ እንዲሆን እንደሚሰራም ተመላክቷል።
በ-አብረሃም በለጠ












