በይሮፓ ሊግ ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ፖርቶ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በ3ኛ ዙር የይሮፓ ሊግ ጨዋታዎች 12 መርሃግብሮች በተለያዩ ሃገራት እና ስታዲየሞች ሲደረጉ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት በሜዳው ፖርቶን ምሽት 4 ሰዓት የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።
ከቀናት በፊት ተሰናባቹን አሰልጣኝ አንጅ ፖስትኮግሉን በመተካት የተሾሙት ሴን ዳይች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፣ ቡድኑን ወደ አሸናፊነት የመመልስ እዳ ተጥሎባቸዋል። ፎረስት በውድድር ዓመቱ እስካሁን ሁለት አሰልጣኞችን ያሰናበተ ደካማ የውድድር ዓመት ጅማሮን አድርጓል።
በይሮፓ ሊግ እስካሁን ካደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ አቻ ወጥቶ በአንዱ ሲሸነፍ፣ ተጋጣሚው ፖርቶ በአንጻሩ በሁለቱም ባለድል ሆኗል። በምሽቱ ጨዋታ የአሸናፊነት ቅድመ ግምት የተሰጠው ፖርቶ ሉክ ዲዮንግ እና ቶማስ ፔሬዝን በጉዳት ሲያጣ፣ በተመሳሳይ ባለሜዳው ፎረስት የክሪስ ውድ እና ኦላ አይና ግልጋሎትን አያገኝም።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ ጎ ሄድ ኤግልስ አስቶን ቪላን በሜዳው ሲያስተናግድ፣ ኦሎምፒክ ሊዮን ከ ባዝል፣ ሮማ ከ ቪክቶሪያ ፕላዛ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












