27ኛው አመታዊ የጤና ዘርፍ ጉባዔ በጅማ ከተማ “ዘላቂ ኢንቨስትመንት እና ኢኖቬሽን ለጠንካራ የጤና ስርዓት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባዔው ላይ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዷል። የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ መታዊው የጤና ዘርፍ ጉባዔ ሲጠናቀቅ በርካታ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ከነዚህም መካከል የጤና ባለሙያዎችን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይጠበቃሉ ብለዋል። ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የጤናውን ዘርፍ ይበልጥ ለማዘመን እና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚረዱ ውሳኔዎች በጉባዔው መጨረሻ እንደሚወሰን አስረድተዋል።
በጅማ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው 27ኛው የጤና ዘርፍ መታዊ ጉባዔ ትናንት የተጀመረ ሲሆን በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።
በ – አክረም ኑርያ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












