ማርክ አንድሬ ቴርስቴገን በጥር የዝውውር መስኮት ከባርሴሎና ሊለቅ እንደሚችል ተዘገበ።
ጀርመናዊው ግብ ጣባቂ ከአስርት አመታት በኋላ ከካታላኑ ክለብ በጥር ሊለያይ እንደሚችል ስካይ ስፖርት ዘግቧል። ቴርስ ቴገን ያለፉትን አመታት በጉዳት እየተፈተነ የሚገኝ ሲሆን፤ ተተኪ ግብ ጠባቂ ይሆናል በሚል ዮሃን ጋርሺያ መምጣቱን ተከትሎም በክረምት ይለቃል በሚል ሲጠበቅ ቆይቷል።
ጀርመናዊው ግብ ጠባቂ ከክለቡ ሃላፊዎች ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ ውዝግብ ውስጥ መግባቱም በባርሴሎና አያቆየውም በሚል ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል። የስፔን ሚዲያዎችን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ስካይ ስፖርት ቴር ስቴገን ከፊታችን ባለው የጥር የዝውውር መስኮት በውሰት ወይም በቋሚ ዝውውር ብሉግራናዎቹ ይለቃል ብሏል።
የ33 አመቱ ቴርስቴገን እስካሁን በባርሴሎና ማለያ በ422 ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ የቻለ ሲሆን፤ በ175 ጨዋታዎች ግቡን ሳያስደፍር መውጣት ችሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












