በስፔን ላሊጋ ባርሴሎና ከሪያል ኦቪዬዶ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በላሊጋው የ6 ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲደረጉ ባርሴሎና ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ሪያል ኦቪዬዶን ይገጥማል። ባርሳ በደረጃ ሰንጠረዥ ከማድሪድ በ5 ነጥብ አንሶ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ምሽት 4፡30 የሜደረገውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ነጥቡን ማጥበብ ያስችለዋል።
የካታላኑ ክለብ እስከሁን ባደረጋቸው 5 ጨዋታዎች በ4ቱ ድል ሲያደርግ በአንዱ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል። በአንጻሩ የሳንቲ ካዞርላው ኦቪዬዶ ካለፉት 5 ጨዋታዎች በ4 ቱ ሽንፈት በማስተናገዱ የዛሬውን ጨዋታ ባርሳ እንደሚያሸንፍ ግምት እንዲሰጠው አስችሏል።
አሰልጣኝ ሃንሲ ፍሊክ በምሽቱ ጨዋታ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን በጉዳት ሳቢያ ግልጋሎታቸውን የማያገኙ ይሆናል። ጋቪ አስቀድሞ በገጠመው ጉዳት ከቡድን ስብስብ የተቀነሰ ሲሆን፣ ላሚን ያማል፣ ፈርሚን ሎፔዝ እና አሌክስ ባልዴም በገጠማቸው ጉዳት በምሽቱ ጨዋታ አይሰለፉም ተብሏል።
ከባርሳና ኦቪዬዶ ጨዋታ አስቀድሞ በሌላ የ6 ሳምንት መርሃ ህብር ኦሳሱና ከ ኤልቼ ምሽት 2፡30 ይጫወታሉ።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












