የአስቶን ቪላ የስፖርት ዳይሬክተር ሞቺ ክለቡን መልቀቃቸው ተገለጸ።
አስቶን ቪላ በያዝነው የውድድር አመት መጀመሪያ እያስመዘገበ ያለውን ደካማ ውጤት መነሻነት የስፖርት ዳይሬክተሩ ራሞን ሮድሪጌዝ ሞቺ ከሃላፊነት መነሳታቸው ታውቋል። ቪላ አምስተኛ ሳምንት በደረሰው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 3 ነጥብ ብቻ በመያዝ 18ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ በካራባኦ ዋንጫም በብሬንትፎርድ ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።
የውጤት መጥፋቱን ተከትሎ ሞቺን ከሃላፊነት ያነሳው ቪላ በቀጣይ ማንን በቦታው ይሾማል የሚለው እየተጠበቀ ይገኛል። ስፔናዊው ሞቺ ክለቡን የተቀላቀሉት በ2023 ሴቪያን በመልቀቅ ሲሆን፤ በአሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬ ጥቆማ መቀጠራቸው ይታወሳል።
ቪላ ባለፉት ሁለት የውድድር አመታት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ያስቻሉ እንደ አማዱ ኦናና ያሉ ተጫዋቾችን ማስፈረማቸው አይዘነጋም። በተጠናቀቀው የዝውውር ገበያም ሃርቪ ኤሊየት እና ጄደን ሳንቾ የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ አምጥተዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












