የእስራኤልና ሶሪያ ወደ ጠረጴዛ መምጣት እና መወያየት ወደ አፉጣኝ የደህንነት ስምምነት ሊያመራ ይችላል ሲሉ የሶሪያው ፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻራ ገለፁ።
በአልበሽር አስተዳደር ስር ለበርካታ አመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትታመስ የቆየችው የሶሪያው መሪ አህመድ አል ሻራ የደህንነት ጉዳይን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታን አድርገዋል። የሶሪያና እስራኤል የ1974 ስምምነት ካበቃበት ጊዜ አንስቶ ቴላቪቭ በተለያዩ የሶሪያ ግዛቶች ጥቃትን ፈፅማለች፤ በርካታ ንፁሀንና ወታደሮች ሞተዋል።
እስከ አለፉት ጥቂት ወራት የቀጠለው የእስራኤል ድርጊት ለማስቆም አዲሱን የሶሪያ መንግስት የምትደግፈው አሜሪካ ሀገራቱ የደህንነት ስምምነት ላይ እንዲደርሱ በአሸማጋይነት ለመስራት መሞከሯን አህመድ አል ሻራ ተናግረዋል።
አል ሻራ አሜሪካ በሶሪያ ላይ ምንም አይነት ጫና እያሳደረች አይደለም ይልቁን በቴላቪቭና በደማስቆ መካከል የደህንነት ስምምነት እንዲደረስ እየሰራች መሆኑን አክለዋል። ምን አልባትም ሊደረገው የሚችለው ስምምነት የእስራኤልን ተደጋጋሚ የሶሪያን የአየር ክልል መጣስ የሚያስቆም መሆን ይገባዋልም ብለዋል።
በሀገራቱ መካከል ደህነትን መሰረት አድርገው የሚከወኑ ማንኛውም ስምምነቶች ወደ ሌሎች ውይይቶችና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ሊያመሩ እንደሚችሉ ተስፉቸውን ገልፀዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












