ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ እንግሊዝ ገብተዋል።
በማዕከላዊ ለንደን ሲደርሱም አስገራሚ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ትራምፕ እና ባለቤታቸው ሜላኒያ ለንዶን ዊንፊልድ ሀውስ መገባታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል። ከ1947 አንስቶ በዩናይትድ ኪንግደም የአሜሪካ አምባሳደር መኖሪያ ሆኖ የሚያገልግል ታሪካዊ ቤትም ነው ዊንፊልድ።
ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለሁለተኛ ጊዜ ያልተጠበቀ ጉዞ ዶናልድ ትራምፕ ሲያደርጉ ነውም ተብሏል። ፕሬዚዳንቱና ባለቤታቸው ሜላኒያ ከኤር ፎርስ ዋን ወርደው በማሪን ዋን ሄሊኮፕተር ወደ ማዕከላዊ ለንደን አቅንተዋል።
ከሰዓታት በኋላ ንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊ ፕሬዚዳንት ትራምፕን በዊንድሰር ካስትል ያገኙቸዋል። ሐሙስ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ጋር ተገናኝተው በበርካታ ጉዳዮች ላይ ሪፐብሊካኑ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
ትራምፕን ወደ ዩኬ ለሁለተኛ ጊዜ ስልጣን ላይ እያሉ የተጓዙ የመጀመሪያው የአሜሪካ መሪም ጉዞው ያደርጋቸዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነገ ትልቅ ቀን ይሆናል ከማለት ውጭ ዝርዝር ሀሳብ በጉዟቸው ዙሪያ ላይ አልሰጡም።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












