ህንድ የሩሲያን እና ቤላሩስን የጦር ልምምድ መቀላቀሏ ተገለጸ።
ህንድ ከአሜሪካ ጋር በንግድ ጦርነት ውስጥ ባለችበት እና ሩሲያ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት ጋር ፍጥጫ ውስጥ በገባችበት ሰዓት የተደረገ ልምምድ ነው። የህንድ ወታደሮች በዛፓድ (ምዕራብ) 2025 የጦር ልምምድ ላይ መሳተፋቸው በኔው ደልሂ እና በሞስኮ መካከል ያለው ትሥስር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መሄዱን ያሳያል ተብሏል።
ስልሳ አምስት የጦሩ ዓባላት በዛፓድ -2025 የአምስት ቀናቱ ልምምድ ላይ መሳተፋቸውን የህንድ መከላለያ ሚኒስቴር አሳውቋል። ሚኒስክ እና ሞስኮ የጦርነት ጊዜ ዝግጅታቸውን ለመፈተሽ ያደርጉት ያለው ልምምድ ኔቶን ሳይቀር ስጋት ውስጥ ከቶት ሰንብቷል።
በልምምዱ ላይ 100,000 ወታደሮች የታዪ ሲሆን ኑክሌር አቅም ያላቸው የጦር ጀቶች መሳተፋቸው ደግሞ ቀጠናውን ጫና ውስጥ አስግብቶታል። “የመጨረሻውን ዛፓድ(ምዕራብ) 2025 ልምምድ አድርገናል “ሲሉም ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፒቲን ይፋ አድርገዋል።
ከህንድ ባሻገር የኢራን ፣ባንግላዴሽ፣ ቡርኪና ፋሶ ፣ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የየማሊ ሀይሎች ልምምዱን መቀላቀላቸውንም የክሬምሊን መረጃ ያሳያል ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












