የአትሌቲኮ ማድሪዱ የአጥቂ መስመር ተሰላፊ ጁሊያን አልቫሬዝ በጉዳት ምክንያት ከነገው የሊቨርፑል ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተገለፀ።
በሳምንቱ መጨረሻ በላሊጋው የአመቱን የመጀመሪያ ድል ቪያሪያል ላይ በመቀዳጀት ጥሩ ሳምንት ማሳለፍ የቻሉት ሮጂ ብላንኮዎቹ መንደር ሁለት አዳዲስ የጉዳት ዜናዎች ተሰምቷል።
አትሌቲኮ ማድሪድ በነገው እለት በሻምፒዮንስ ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከእንግሊዙ ሊቨርፑል ሲያደርግ አርጀንቲናዊው አጥቂ ጁሊያን አልቫሬዝ እና ተከላካይ ዳቪድ ሃንኮ በጉዳት ከጨዋታው ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል።
በቪያሪያሉ ጨዋታ የጉልበት ጉዳት ያስተናገደው አልቫሬዝ በመጀሪያው አጋማሽ ነበር በአሌክሳንደር ሶርሎት ተቀይሮ ለመውጣት የተገደደው። አልቫሬዝ ከማንችስተር ሲቲ ለቆ ሮጂ ብላንኮዎቹን ከተቀላለቀለ በኋላ ወሳኝ ተጨዋች መሆን የቻለ ሲሆን በ 57 ጨዋታዎች 29 ጎሎችን አስቆጥሮ 8 ኳሶችን ለግብ ማመቻቸት ችሏል።
ከጁሊያን አልቫሬዝ እና ዴቬን ሃንኮ በተጨማሪ ቲያጎ አልማዳ ፣ ሆዜ ማሪያ ሄሚኔዝ እና አሌክስ ባዬና የነገው ምሽቱ ጨዋታ በጉዳት እንደሚያመልጣቸው ይጠበቃል።
በ- ዳንኤል መምሩ












