አዲስ ከተመረጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጋር ዛሬ ተወያይተናል።
በዚሁ አጋጣሚ ሀገር አቀፍ የመጅሊስ ምርጫው በተሳካ መልኩ እንዲካሄድ በማድረጋቸው ለህዝበ ሙስሊሙና ለምክር ቤቱ አመራሮች አድናቆቴን ለመግለጽ እወዳለሁ። የመጅሊስ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ፣ አካታችና አሳታፊ በሆነ መልኩ መከናወኑ ትምህርት የሚሰጥ ነው።
መንግሥት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ተቀራርቦ የሚሠራ ሲሆን በሚያስፈልገው ሁሉ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ያደርጋል። ለምክር ቤቱ አመራሮች መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው እመኛለሁ።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












