የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በእስራኤል ተገናኝተዋል፡፡
በኔታንያሁ እና በሩቢዮ መካከል ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ በዋናነት የእስራኤል ጦር የጋዛ ከተማን ለመቆጣጠር ማቀዱን እንዲሁም እስራኤል በኳታር ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ነው፡፡
ሩቢዮ ወደ እስራኤል ከመሄዳቸው በፊት እንደገለጹት፣ ዶናልድ ትራምፕ በጥቃቱ ደስተኛ አለመሆናቸውን ነገር ግን አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት አያሻክረውም ብለዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በእስራኤል የሚገኘውን ምዕራባዊ ግንብ ጎብኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ኔታንያሁ እንደገለጹት፤ በአሜሪካ እና በእስራኤል መካከል ያለው ጥምረት “እንደ ቅዱሱ ስፍራ ድንጋዮች ዘላቂ ነው፤ ደግሞም ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል እስራኤል የበኩሏን ታደርጋለች” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












