የመርሲሳይዱ ክለብ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ለረጅም ጊዜ በክለቡ እንዲቆይ የሚያስችለውን ውል ለማስፈረም በሂደት ላይ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
የ31 አመቱ ፒክፎርድ አሁን ላይ እስከ አውሮፓውያኑ 2027 የሚያቆይ ኮንትራት ቢኖረውም፤ ቶፊዎቹ የተሻለ ክፍያ የሚያስገኝለትን ውል ለመስጠት ተዘጋጅተዋል። ግብ ጠባቂው ከተከላካዩ ጃሬድ ብራዝዋይት በመቀጠል ከፍተኛ ደመወዝ የሚከፈለው ሲሆን፤ አሁን የቀረበለት ክፍያ የመጀመሪያ ያደርገዋል ተብሏል።
ኤቨርተን በሁለት አጋጣሚዎች ከሊጉ ላለመውረድ በተጫወተበት ወቅት የፒክፎርድ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑ እና ከክለቡ ወሳኝ ተጫዋቾች አንዱ መሆኑን አሳይቷል። ተጫዋቹ ክለቡን የተቀላቀለው በአውሮፓውያኑ 207 ሲሆን 322 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 90 ጊዜ ግቡን ሳያስደፍር ወጥቷል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












