የሰሜን ለንደኑ ቶተንሃም ባለቤቶች ክለቡን ለመሸጥ ፍላጎት እንዳላቸው እንደተጠየቁ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ከቀናት በፊት የክለቡ ከፊል ባለድርሻ እና ሊቀመንበር የሆኑት ዳኔል ሌቪ ከ25 አመት ቆይታ በኋላ መልቀቃቸውን ተከትሎ የክለብ አሻሻጭ ደላሎች የስፐርስ ባለቤቶችን አነጋግረዋል። ተሰናባቹ ሊቀመንበር ዳኔል ሌቪ የክለቡን ፋይናንሳዊ ጥቅም በማስጠበቅ የሚደነቁትን ያህል፣ የስፖርት ደላሎች መፈንጫ እንዳይሆንም ሲከላከሉ ቆይተዋል።
የቶተንሃምን ባለቤቶች አግኝተዋል የተባሉት ደላላ አማንዳ ስታቭሊ ሲሆኑ፣ አሜሪካውያኑ የልዊስ ቤተሰቦች ጥያቄዋን ውድቅ አድርገዋል ተብሏል። አማንዳ ስታቭሊ ከዚህ ቀደም የሚታወቁት የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በኒውካስትል ዩናይትድ የ80 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ እንዲገዛ ባደረጉት አስተዋጽኦ ነበር።
ወይዘሮዋ አሁንም በተመሳሳይ ቶተንሃምን ለማሻሻጥ የጠየቁት የአረብ ባለሃብቶችን በመያዝ ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












