የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ጊቪር ጋር በመሆን የተኩስ ጥቃት በተፈጸመበት ቦታ ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ።
በእስራኤል በደረሰ የተኩስ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ሲገደሉ ሰባት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡
የእስራኤሉ ማጌን ዴቪድ አዶም አምቡላንስ አገልግሎት ሟቾቹን በ30ዎቹ እና በ50ዎቹ እድሜ ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ተናግረው በተኩሱ የቆሰሉ ሰዎችም ወደ አካባቢው ሆስፒታሎች መወሰዳቸውን አብራርቷል፡፡
የእስራኤል ፖሊስ እንዳስታወቀው በከተማዋ ሰሜናዊ ዳርቻ በሚገኘው ራሞት አካባቢ ላይ ሁለት አሸባሪዎች አውቶቡስ ማቆሚያ ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ቢያብራራም የትኛዉም ታጣቂ ቡድን ግን ሀላፊነት አልወሰደም፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












