የቀድሞው ታሪካዊ ተጫዋች ዳኒ መርፊ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘቡን ተጭበርብሮ ማጣቱን አስታወቀ፡፡
የቀድሞው የሊቨርፑል እና ፉልሃም ታሪካዊ ተጫዋች በኢንቨስትመንት ስም በተቀነባበረ ወንጀል 5 ሚሊዮን ፓውንድ እንደተወሰደበት ገልጿል።
ዳኒ መርፊ በደረሰበት ጥቃት በመበሳጨት በአልኮል ሱስ መዘፈቁን እና ቁማር መጀመሩንም በመግለጽ፤ ለተበደልኩት በደል ፍትህ ይሰጠኝ ሲል ከቶክ ስፖርት ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።
መርፊን አታሏል የተባለው ኪንግስ ብሪጅ አሴት የተባለው ተቋም፤ ከአውሮፓውያኑ ከ1990 እስከ 2ሺዎቹ አጋማሽ ለበርካታ ሰዎች አክሲዮን በመሸጥ ከ417 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ሰብስቧል።
ይሁን እንጂ ከቅርብ አመታት ወዲህ ከስሬያለሁ በሚል በማሳወቁ የብዙ ሰዎች ገንዘብ ቀልጦ መቅረቱ ተዘግቧል። ፖሊስ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ያለ ሲሆን፤ የበርካታ አመት ወደኋላ መመለስን የሚጠይቅ ጉዳይ በመሆኑ ጊዜ እንደሚወስድ ገልጿል።
በዚሁ ተመሳሳይ ድርጅት የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ማይክል ቶማስም ገንዘቡን እንደተበላ ተገልጿል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












