በቀጣይ መስከረም ወር በአንዳንድ ስፍራዎች የመሬት መንሸራተትና በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ እንደሚጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የመስከረም ወር የሚቲዎሮሎጂ ትንበያን እንደገለጸው፤ በመስከር ወር በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች አልፎ አልፎ ከባድ ዝናብ ይዘንባል። በሚጥለውም ዝናብ የመሬት መሸራተት ሊከሰት ይችላል፡፡
በመስከርም ወር አልፎ አልፎ በሚጥለው ከባድ ዝናብ ተዳፋትና ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ የአፈር መሸርሸር፣ በእርሻ መሬቶች ላይ ውሀ የመተኛት፣ በደርሱ ስብሎች ላይ ጉዳት ሊከሰት ይችላል ብሏል፡፡
በሰብሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል አርሶ አደሮች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ጥንቃቄ ማደርግ አለባቸው ሲል አሳስቧል፡፡
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












