ፕሬዚዳንት ቮሎድሜር ዘለንስኪና ምዕራባውያን ደጋፊዎቻቸው በሩሲያ ጉዳይ ላይ በፈረንሳይ ተወያዩ።
የዩክሬን ደጋፊ ምዕራባውያን አገራት ‘የፈቃደኞች ጥምረት’ በፓሪስ ኤልዚ ቤተ መንግስት ተገናኝተዋል። የአውሮፓ ህብረት ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሊየን፣ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሜር ዘለንስኪ፣ የቤልጂዬም፣ ፖላንድ፣ ፊንላንድና የፈረንሳይ መሪዎች በጥልቀት መክረዋል።
ኪዬቭም ምዕራቡ ዓለም የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣት አብዝታ በመጠየቅ ላይ ስትሆን ዶናልድ ትራምፕም ከጎኗ እንዲቆሙ በመወትወት ላይ ናት ተብሏል ። ምንም እንኳን የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት(ኔቶ)ን መቀላቀል አታስበው ቢልም ዘለንስኪ ከመጠየቅ ወደ ኋላ አላሉም።
ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ብርቱ ውይይት ያደረጉትም በሩሲያ ላይ ጫና ለመፍጠር ነው ተብሏል። የቀድሞው የፖላንድ መሪ ዱዳ የዘለንስኪ ፍላጎት ኔቶን ቀጥታ ጦርነቱ ውስጥ ማስገባት ነው ማለታቸውም የተለያዪ ጥርጣሬዎችን በምዕራቡ ዓለም አስነስቷል ተብሏል። ሩሲያ ላይ ፖላንድ ጦር እንድትከፍትም ዘለንስኪ ጠይቀውኝ ነበር ብለዋል ዱዳ።
አር ቲ እንዳስነበበው
በ-ቢኒያም ካሴ












