እስራኤል ጋዛ ከተማን 40 በመቶ መቆጣጠሯን የአገሪቱ ጦር አስታወቀ።
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ በአሁኑ ሰዓት በሰሜናዊ ጋዛ አብዛኛውን አካባቢ በመቆጣጠር ላይ ነን ብለዋል። ከሰሜናዊ ጋዛ ባሻገር ጎረቤት ዘይቱን እና ሼይክ ራድዋን አካባቢዎችም ሰለባ ሆነዋል።
ዘመቻው በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ብርጋዴር ጀነራል ኤፌ ደፍሪን ይፋ ያደረጉ ሲሆን፣ እስራኤል በጋዛ የምታደርሰው ጥቃት ዓለም አቀፍ ውግዘትን እያስከተለባት ይገኛል ተብሏል።
ጀነራሉ እንዳሉት እስራኤል ይህን ጦርነት የምታቆመው ታጋቾች ሲለቀቁና ሃማስ ጋዛን ማስተዳደር ሲሳነው ብቻ ነው። ምንም እንኳን እስራኤል በአጭር ጊዜ ውስጥ ታጋቾችን አስለቅቃለሁ የሚል አቋም ቢኖራትም ያለሃማስ ፈቃድ እስካሁን ማስለቀቅ አለመቻሏ ውጥረቱ ሊከፋባት እንደሚችል ይጠቁማል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለፍስጤም አገርነት ዕውቅና የሚሰጡ አገራትን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ መውቀሳቸው ተሰምቷል ። ፈረንሳይ በፍልስጤም ዕውቅና ሳቢያ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ትችት ከተሰነዘረባቸው አገራት ውስጥ ግንባር ቀደም ናት ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












