ተሰናባቹ የባየር ሊቨርኩሰን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ ጠቀም ያለ ካሳ እንደተከፈላቸው ተሰማ።
የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ እና አያክስ አሰልጣኝ ባየር ሙኒክን በተረከቡ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ከሃላፊነት መነሳታቸው ይታወሳል። ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ በጀርመኑ ክለብ ውላቸው መቀደዱን ተከትሎ 6 ሚሊዮን ዩሮ ካሳ እንደተከፈላቸው ቢልድ ጋዜጣ ዘግቧል።
ቴንሃግ የተሰጣቸው ካሳ ሲሰላ በቀን 100ሺ ዩሮ በመሆኑ እና ከፍተኛ መሆኑ ቢያነጋግርም፤ ለስራ ታሪካቸው ውድቀት መሆኑ ተመላክቷል። አሰልጣኙ ከአመታት በፊት በኔዘርላንዱ ክለብ አያክስ አስደናቂ ቡድን በመስራት ሪያል ማድሪድን በመሳሰሉ ክለቡች ተፈላጊ ሆነው እንደነበር አይዘነጋም።
ሆኖም በእንግሊዝ ማንችስተር ዩናይትድን በማሰልጠን ውድቀት ማሳየት በመጀመራቸው የቀድሞ ዝናቸው ደብዝዟል። ቴንሃግ አሁን ላይ የእረፍት ጊዜያቸውን በማሳለፍ ላይ ሲሆን በቀጣይ የትኛውን ክለብ ያሰለጥናሉ የሚለው የሚጠበቅ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












