የባሕል ጥበባትና ስፖርት ሚዲያ ፎረም ምስረታ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የኢፌዴሪ ባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የተቀናጀ ስራን ለመስራት ያስችለኛል በሚል የሚዲያ ፎረም ለመመስረት ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፤ ሚኒስቴሩ ዘርፉን በቅርበት ለመከታተል ያስችለው ዘንድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በይበልጥ የሚያቀራርብ የሚዲያ ፎረም መመስረት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አንስተዋል።
በስፖርት ዘርፉ የገጠመውን ስብራት ለመለየት፣ ባሕልንም በማስተዋወቅ እና ማሳደግ ላይ የሚስተዋለውን ክፍተት ለመቅረፍ ተቀራርቦ መነጋገር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም በፎረሙ ላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸው የተደራጀ እውነተኛ መረጃን ለማግኘትና ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ያስችላቸዋል ብለዋል።
በውይይት መድረኩ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የስራ አመራሮች፣ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ውይይቱ በመቀጠል ላይ ይገኛል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












