ኢትዮጵያዊያን በህዳሴው ግድብ ላይ ያላቸውን አስተያየት፣ የተሰማቸውን ስሜትና መልእክት በ8120 የአጭር መልዕክት ማስተላለፊያ ኮድ የሚልኩበት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት “የትውልድ አሻራ – ዲጂታል የብስራት መልዕክትና ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት”ን በሰጠው መግለጫ አስተዋውቋል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የእጅ ስልኩን በመጠቀም በ 8120 ላይ በ 20 ብቻ ለግድቡ ድጋፍ በማድረግ የህዳሴው ግድብን በተመለከተ ያለውን መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚችል ተመላክቷል።
መርሃ ግብሩ ከነሐሴ 27/2017 ዓ.ም. እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም. የሚቆይ መሆኑን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መግለጫ ይጠቁማል። በአጭር መልዕክት ማስተላለፊያ ኮዱ ላይ ያሉትን የተለያዩ አማራጮችን በመጫንም ከ 5 ብር እስከ 100 ብር ለግድቡ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልም ተመላክቷል።
በ – አብርሃም በለጠ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












