በመጪው መስከረም ወር በአማራ እና ኦሮሚያ ክልልሎች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ይጀመራል ተባለ።
የአማራ ክልል የሰው ሃብትና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ባንቺአምላክ ገ/ማርያም፣ በቀጣይ ዓመት መስከረም ወር ጀምሮ በባሕርዳር፣ ደሴና ጎንደር ከተሞች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ሥራ ይገባል ብለዋል።
በቀጣይ ደግሞ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ኮምቦልቻ እና ደብረ ታቦር ከተሞች በሁለተኛ ዙር አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ነው ያሉት፡፡
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በኦሮሚያ 4 ከተሞችም በተመሳሳይ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቅቋል ያሉት የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ዳምጠው ገመቹ ናቸው።
አገልግሎቱ የሚጀመርባቸው ከተሞች አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሸገር እና ሻሸመኔ መሆናቸውንመእ አቶ ዳምጠው ተናግረዋል። በቀጣይ በሁለተኛ ዙር በ19 ከተሞች አገልግሎቱን የማስፋት ሒደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያረጋገጡት፡፡
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












