የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሀገራዊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ስነ-ምህዳርን ለማስፋት የኢንተርፕረነርሺፕ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ በማዘጋጀት ከባለድርሻ አካላት፣ ከስራ ፈጣሪዎችና የኢንተርፕረነርሺፕ ሥነ ምህዳር ላይ ሚና ካላቸው አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ያላትን አቅሟች በማሰባሰብ እውቀትን በመደመር እንዲሁም በተለያዩ የስራ ስምሪት ላይ ያሉ ዜጎች ኢንተርፕረነር ለመሆን ያላቸውን ፍላጎት ከግብ ለማድረስ ምቹ ስነምህዳር ለመፍጠር ይህ ፈቂቅ ፖሊሲ ወሳኝ ሚና እንዳለው በመድረኩ ተነስቷል።
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ከሚል ከስራ ፈጣሪ ዜጎች ጋር በቅንጅት ለመስራት ረቂቁ ምቹ እድልን ይፈጥራል ያሉ ሲሆን የስራ ፈጣሪዎቹ በሚሄዱበት የመንግስት እንዲሁም የአገልግሎት ተቋማት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና አይሆንም የሚባሉ ገፊ ምላሾችን ወደ ይችላሉ ለመቀየር ያስችላል ብለዋል።
በመድረኩ ከዚህ ቀደም ኢንተርፕረነር ለሆኑ ዜጎች በቂ ትኩረት ያልተሰጠቸው በመሆኑ በዘርፉ ውጤታማ እና በርካታ የስራ ፈጣሪ ትውልዶችን ማፍራት ስላለመቻሉ ተነስቷል።
የይቻላል አስተሳሰብን በማጎልበትና ኢንተርፕረነራዊ ዕድሎች ለሁሉም እንዲፈጠር ለማድረግ አካታች ኢንተርፕረነርሺፕን ማሳደግና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሽግግሮችን ለማፋጠን ይህ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።

በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ( ዶ/ር)፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
የመጀመሪያው የኢንተርፕረነርሺች ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ስምንት ዋና ዋና ማዕቀፎችን የያዘ ሲሆን ከምሁራን፣ ከዘርፉ ባለሙያዎች እና ተዋናዮች የሚነሱ ሀሳቦችን በማካተት ረቂቅ ሰነዱ የሚጎለብት ይሆናል።
በ _ሀሴት ሃይሉ












