ታዳጊው ተጫዋች በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ስር በቂ የመሰለፍ ዕድል አለማግኘቱን ተከትሎ የዝውውር ገበያው ከመዘጋቱ በፊት ከኦል ትራፎርድ ሊለቅ ይችላል ተብሏል።
ኮቢ ሜይኑ በአሰልጣኙ እምነት የብሩኖ ፈርናንዴዝ ተጠባባቂ እንዲሆን ቢታሰብም፤ በተጫዋቹ በኩል አሳማኝ ሆኖ አልታየም። በቀደመው ጊዜ ሁለቱ ተጫዋቾች አብረው መጫወት እንደሚችሉ የታየ በመሆኑ ተጠባባቂ መደረጉን ታዳጊውን አላሳመነውም ተብሏል።
ዩናይትድ በፕሪምየር ሊግ ከአርሰናል እና ፉልሃም ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች አለመሰለፉ፤ በውድድር አመቱ በቂ እድል እንደማይሰጠው እና አሰልጣኙም በርሱ ላይ ያላቸው እምነት መደብዘዙን ያሳያል በሚል ለመልቀቅ ወስኗል እስየተባላ ይገኛል።
የ20 አመቱ እንግሊዛዊ አማካኝ በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ሃገሩን መወከል የሚፈልግ በመሆኑም ዕድል ወደሚያገኝበት ክለብ መጓዝ ይፈልጋል እየተባለ ነው። የዝውውር ገበያው ሊዘጋ 7 ቀናት የቀሩት ሲሆን፤ እንደ ቼልሲ እና ቶተንሃም ያሉ ክለቦች ተጫዋቹን ይፈልጋሉ በሚል ተዘግቧል
ኮቢ ሜይኑ በዋናው ቡድን የመሰለፍ ዕድል ከተሰጠው ወዲህ 72 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 7 ጎሎችን ሲያስቆጥር፣2 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












