የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ከመጪው ስብሰባ ኋላ ጦርነቱን ካላስቆመ ዉጤቱ የከፉ ይሆናል አሉ።
ትራምፕና ፑቲን ከሩሲያ ዩክሬን ጦርነት መጀመር ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ በነገው እለት አርብ በአላስካ እንደሚገናኙ ይታወቃል። ከዚህም ስብሰባ አስቀድሞ በትላንትናው እለት ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ እንዲሁም ከሌሎች የአውሮፓ መሪዎች ጋር የቪዲዮ ስብሰባን አካሂደዋል።
በጀርመኑ መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርዝ አስተባባሪነት በበርሊን በተደረገው የኦንላይን ስብሰባ መልካም የሚባል እንደነበር ዶናልድ ትራምፕ ገልጸዋል። ትራምፕ አክለውም በመጪው አርብ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ ላይ የሰላም ስምምነት ከተደረገ ኬቭን ያገለለ ሊሆን እንደማይችል አስታውቀዋል።
እንዲሁም መጪው ስብሰባ በመልካም መንገድ ከተጠናቀቀ በአፉጣኝ የሩሲያና ዩክሬን መሪዎች ጋር በአንድ ላይ ለመገናኘት እንደሚያመቻቹ ቃል ገብተዋል። ሆኖም ከውይይቱ ኋላ ፑቲን ጦርነቱን ለማስቆም ካልወሰነ ውጤቱ የከፉ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፤
ዘባው የአልጀዚራ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












