የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦኤም ባወጣው መረጃ መሰረት ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ወደ 3000 የሚጠጉ ስደተኞች የሜዲትራኒያን ባህር ለማቋረጥ ሲሞክሩ እንደሞቱ ይገመታል ብሎዋል።
ይህ ሌሎች ብዙ ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀ የሚጠቁሙ መረጃዎች አመላካች እንደሆነ ይናገራል። አብዛኞዎቹ የሞቱ ሰዎች ሰሜን አፍሪካን ከጣሊያን ጋር በሚያገኘው የመካከለኛው ሜዲትራኒያን መንገድ ላይ መሆኑን IOM ገልጿል።
የዘንድሮው የሟቾቹ ቁጥር እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2015 በተመሳሳይ ወቅት ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች ቁጥር በእጅጉ ከፍ ያለ እንደሆነም ተመላክቷዋል። ነገርግን ይህ ፍሰት በመጋቢት ወር የተቋረጠ ሲሆን በርካታ ሀገራት ድንበሮቻቸውን ለመዝጋት መወሰናቸውን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ከቱርክ ጋር የስደተኞችን ፍሰት በተሻለ ለመቆጣጠር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው
በ-አማኑኤል ምትኩ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












