ጣሊያናዊው አትሌት ማቲያ ዴበርቶሊስ በውድድር መሃል ድንገት ከወደቀ ከሶስት ቀናት በኋላ ሕይወቱ አልፏል።
ባሳለፍነው ሳምንት አርብ በቻይና በተደረገው የመካከለኛ ርቀት የጎዳና ሩጫ የተካፈለው አትሌቱ በውድድሩ የተወሰነ ርቀት ከተጓዘ በኋላ በድንገት ራሱን ስቶ በመውደቁ በአንቡላንስ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰድ ተደርጓል።
አትሌት ዴበርቶሊስ በሆስፒታል አስፈላጊው ህክምና እየተደረገለት ቢቆይም በዛሬው ዕለት ህይወቱ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል። የ29 አመቱ አትሌት ድንገተኛ ህልፈት ምንነቱ እስከሁን በግልጽ ያልታወቀ ሲሆን፤ የቀደመ ህመም እንዳልነበረበት ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።
ዴበርቶሊስ ሃገሩን ጣሊያን በተለያዩ ውድድሮች ሲወክል፤ በ2022ቱ የአለም ሻምፒዮና ተካፋይ መሆንም ችሏል። የአለም አትሌቲክስ አዘጋጅ ተቋም ለሟች ቤተሰቦች አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አሳውቋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












