ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “የተወሰነ መሬት ለዩክሬን ለማስመለስ እሞክራለሁ” አሉ።
ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሲገናኙ ትራምፕ የተወሰኑ ግዛቶችን ለማስመለስ ጥረት ያረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትራምፕ “ሩሲያ በርካታውን የዩክሬንን ግዛት ይዛለች፣ ወሳኝ ግዛቶችን ተቆጣጥረዋል፣ የተወሰነውን እንኳን ለማስመለስ እንሞክራለን።” ብለዋል።
“ከፑቲን በኩል ለውጥ ይመጣ እንደሆነም በውይይታችን በ2 ደቂቃ ውስጥ መረዳት እችላለሁ” ያሉት ትራምፕ፣ ስብሰባውን እንደበር ከፋች መድረክ እወስደዋለሁ በሚልም አረጋግጠዋል። በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል የመሬት ልውውጥ ሊኖር እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ሩሲያ ክሪሚያን ጨምሮ ከዩክሬን ከወሰደቻቸው አምስት ግዛቶች ውስጥ የትኛውን ትመልሳለች ስለሚለውም ያሉት ነገር የለም። በተለይም ዩክሬን ከሩሲያ ምንም ዓይነት ግዛት አልጠቀለልኩም የሚል አቋም ላይ መሆንዋ የትራምፕ ውጥን ከባድ ያደርገዋል።
ለዘለንስኪ ደውዬ ውጊያውን ቀጥሉበት አሊያም አሁን መስማማት እንችላለን የሚል ሀሳብ ላጋርም እችላለሁ በሚል መግለጫ የሰጡት ትራምፕ፣ ከፑቲን ጋር ሲገናኙ የሚመዘገበውን ውጤት ለአውሮፓ መሪዎችም አጋራለሁ ብለዋል።
ዶናልድ ትራምፕና ቭላድሚር ፑቲን ዓርብ በአላስካ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቢቢሲ እንደዘገበው።
በ-ቢኒያም ካሴ












