የጣልያኑ ክለብ ተጫዋቹን የመግዛት አማራጭ በተካተተበት የውሰት ውል የማስፈረም ፍላጎት ያለው ሲሆን፤ ማንቸስተር ዩናይትድ በአንፃሩ በቋሚ ዝውውር ድርድሩን የመቋጨት እቅድ ይዟል።
ከፊዮረንቲና ጋር በነበረው የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ጨዋታ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ሆኖ የጨረሰው ሆይሉንድን ለመሸጥ ቀያይ ሰይጣናቱ 40 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከቅዳሜው ጨዋታ በኋላ ሜሰን ማውንትን እንደ ሃሰተኛ ዘጠኝ ቁጥር መጠቀማቸውን በተመለከተ ለቀረበለቸው ጥያቄ “አጥቂ ይዘን ባለመግባታችን ተቸግረናል፤ አዲስ ተጫዋች አለን እሱን ደግሞ እናየዋለን” በማለት የሰጡት አስተያየት ምናልባትም ስለ ሆይሉንድ ያላቸውን እምነት የሚያሳይ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች ተበራክተዋል።
ሆይሉንድ በኦል ትራፎርድ ቆይቶ ለቦታው ለመታገል ቢፈልግም አሁን ያለው እውነታ ግን በክለቡ ከማይፈለጉ ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ነው ሲል ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












