የሰሜን ለንደኑ ክለብ ብራዚላዊውን የክንፍ ተጫዋች ለማስፈረም ሳይጠበቅ ድርድር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
የ21 አመቱን ተጫዋች ለማግኘት ቶተንሃም እስከ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ሊያደርግ ይችላል የተባላ ሲሆን፤ በጉዳት ላጣቸው ማዲሰን እና ክሉሴቭስኪ ተተኪ እንደሚሆን አምኖበታል ተብሏል።
ማንችስተር ሲቲ ሳቪንኒሆን ለመሸጥ ምንም አይነት ፍላጎት ባያሳይም፤ ተጫዋቹ ክለቡን መልቀቅ የሚፈልግ ከሆነ ለማቆየት ተጽዕኖ እንደማያደርግ ተመላክቷል። ሳቪኒዮ ለውሃ ሰማያዊዎቹ ባሳለፍነው የውድድር አመት በ48 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 3 ግቦችን በስሙ አስፍሯል። ለሃገሩ ብራዚልም 13 ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ 1 ጎል ከመረብ አዋህዷል።
የተጫዋቹ ዝውውር በቀጣዮቹ ቀናት እድገት ሊያሳይ እንደሚችል ተዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












