በብራዚል በተካሄደው የወተት ተዋጽኦ ውድድር የጂሮላንዶ ዝርያ ያላት አንዲት ላም 343 ሊትር (90.6 ጋሎን) በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ በማምረት አዲስ ሪከርድ አስመዝግባለች።
የጂሮላንዶዝርያ ያላቸው ላሞች የሚያስደንቅ እና ከፍተኛ የወተት ምርት እንዳላቸው ይነገራል። ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህን አይነት ዝርያ ያላቸው ላሞች በቀን ከ100 ሊትር (26.4 ጋሎን) ወተት በላይ አምርተው አያቁም ነበር።
በደቡባዊ ሚናስ ጌራይስ በዴልፊም ሞሬራ ግዛት በተካሄደው በዚህ ውድድር የጂሮላንዶ ላም በሶስት ቀናት ጊዜ ውስጥ 343 ሊትር ወተት በማምረት አዲስ ብሄራዊ ክብረ ወሰን ማስመስገቧ አስደናቂ ክስተት ሆኗል።
ገበሬዎች ከብቶቻቸውን ለወተት ውድድሮች ለማዘጋጀት ወራትን እንደሚያሳልፉ እንዲሁም የተስተካከለ አመጋገብን በማሟላት የወተት ምርትን ለመጨመር ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
በብራዚል ውስጥ ለከብቶች የተለየ እንክብካቤ የሚደረግላቸው ሲሆን፤ ከፍተኛ ክብርም አላቸው፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












