የቀድሞው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን እና የቦሩሲያ ቦርትሞንድ አጥቂ በልብ ህመም በ67 አመቱ ማለፉን ዘ ሰን ዘግቧል።
ፍራንክ ሚል በተጫዋችነት ዘመኑ 17 ዋንጫዎችን ማግኘት የቻለ ሲሆን፣ከሁሉ የሚነገርለት ጀርመን በሁለት በተከፈለችበት ዘመን ሶሻሊስት ለሆነው የምስራቅ ጀርመን የአለም ዋንጫን ማስገኘቱ ነው።
ሚል የተጫዋችነት ዘመኑን የጀመረው በትውልድ አካባቢው በሚገኘው ዌስ ኤሰን ክለብ ሲሆን፣በ1981 ወደ ዶርትመንድ በመጓዝ በሲግናል ኤዱና ፓርክ የ8 አመት ቆይታ አድርጓል። የቀድሞው ኮከብ የልብ ህመም የገጠመው ባሳለፍነው የግንቦት ወር በጣሊያን በመዝናናት ላይ እንዳለ ነበር።
ከገጠመው ህመም እንዲያገግም የተለያዩ ሙከራዎች ቢደረጉም እለት በዕለት ተባብሶበት ለህልፈት መዳረጉን ቤተሰቦቹ ለቢልድ ጋዜጣ ተናግረዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












