በአውሮፓውያኑ 1958 በአውሮፕላን አደጋ ያለፉትን የክለቡን ተጫዋቾች ለማሰብ ራሳቸውን “1958” ብለው የሚጠሩት የዩናይትድ ደጋፊዎች ከአርሰናል ጋር በሚደረገው የፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ ሰር ጂም ራትክሊፍን ለመቃወም ተዘጋጅተዋል።
የማንችስተር ዩንይትድ ከፊል ባለድርሻ ሰር ጂም ራትክሊፍ ባሳለፍነው የውድድር አመት የክለቡን ሙሉ አስተዳደር ተረክበው መስራት ከጀመሩ ወዲህ ያስመዘገቡት ውጤት ደጋፊዎቹን እንዳበሳጨ ታውቋል።
ዩናይትድ ከ1931 በኋላ ደካማውን የውድድር አመት ያሳለፈ ሲሆን፣ከየትኛውም የአውሮፓ ውድድር ውጪ ሆኖ አዲሱን የውድድር አመት ይጀምራል።
የቀያይ ሰይጣኖቹ ደጋፊዎች በክለቡ ከፍተኛ ባለድርሻ በሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች ላይ ለአመታት የቆየ ተቃውሞ ያላቸው ሲሆን፤ በብዙ ተስፋ ወደ ክለቡ በመጡት ሰር ጂም ራትክሊፍ ላይ ተቃውሞ አጥራታቸው አስደናቂ ሆኗል።
ሰር ጂም ራትክሊፍ ክለቡን በሜዳ ላይ እና ከሜዳ ውጪ ለማሳደግ፤ ኦል ትራፎርድን እንደ አዲስ ለመገንባት ያላቸውን ዕቅድ በተመለከተም ለአሁኑ ችግር መፍትሄ የማይሆን በሚል ተሳልቀዋል።
በዝውውር መስኮቱ ክለቡ መልቀቅ የሚፈልጋቸውን ተጫዋቾች በጊዜ አለመልቀቁ እና ተጨማሪ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ አለማካተቱ ደጋፊዎችን እንዳበሳጨ በዘገባው ተመላክቷል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












