ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ያደገው በርንሌይ በያዝነው የዝውውር መስኮት ብቻ 10ኛ ተጫዋች ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል።
የ21 አመቱ ኡጉቹኩ ባሳለፍነው የውድድር አመት በውሰት ውል በሳውዝሃምፕተን ያሳለፈ ሲሆን፤ በአሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ የቡድን ስብስብ አለመፈለጉን ተከትሎ ወደ በርንሌይ ያቀናል።
በርንሌይ ለፈረንሳዊው ተጫዋች እስከ 30 ሚሊዮን ፓውንድ ሊከፍል ይችላል የተባለ ሲሆን፣በተርፍሞር የሚያቆየውን የ5 አመት ውል ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።
የአሰልጣኝ ስኮት ፓርከር ቡድን በርንሌይ በፕሪምየር ሊግ ለመቆየት ልምድ ያካበቱትን ካይል ወከር እና አግዜል ቱዋንዜቤን ከዚህ ቀደም ማስፈረሙ ይታወሳል።
ቼልሲ የቡድን ስብስቡን ለማጥበብ በርካታ ተጫዋቾችን በመሸጥ ላይ ይገኛል። ሌላኛውን የአማካኝ ስፍራ ተጫዋች ኬርናን ዴውዝበሪ ሆልን ለኤቨርተን ለመሸጥ በውይይት ላይ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












