በክልሉ ባሉ 7 የአሰሪ ማህበራት አማካይነት የአደራጅ ምክር ቤት አደራጅተው ሲያስተባብሩ የቆዩት ማህበራት የክልላቸውን የአሰሪ ፌዴሬሽን በሀምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የመጀመሪያውን ፌዴሬሽን አቋቁመዋል፡፡
በምስረታ ጠቅላላ ጉባኤም ከ70 በይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በጉባኤውም የክልሉ የስራ እና ክህሎት ቢሮ ተወካይ፤ የሀዋሳ ንግድና ማህበራት ዘርፍ ምክር ቤት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ጉባኤውም የፌዴሬሽኑን ህገ-ማህበር ተወያይቶ ያጸደቀ ሲሆን የፌዴሬሽኑን የቀጣይ 5 ዓመታት የሚመሩ 11 የስራ አመራር ቦርድ አበላትን መርጧል፡፡
በምርጫውም ፦
አቶ ደጀኔ ጌታቸውን – ፕሬዝደንት
አቶ ዮሴፍ ጌታቸውን – ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት
አቶ ብርሀኑ በላይን – ምክትል ፕሬዝደንት
አቶ ጸጋዬ አየለን – ዋና ጸሀፊ
የተከበሩ አቶ ደሳለኝ እጀጉ – አቃቢ-ነዋይ ሲያደርግ
አቶ አብይ ጌታቸው፤ አቶ አቢዮት ጸጋዬ፤ ዶ/ር ፀጋዬ ማቲዎስ፤ ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት፤ ወ/ሮ ወንጌል የሸዋልዑል እና ወ/ሮ ዝናሽ ሲዳ ደግሞ የቦርድ አባል አድርጎ ምርጫውን አጠናቋል፡፡
በመጨረሻም የተመረጡት ፕሬዝደንት ደጀኔ ጌታቸው ማህበራት ሲመሰረቱ ባለው ተነሳሽነት ልክ ወደ ስራም ሲንገባ ጠንክረው በአንድነት እንዲሰሩ መልእክታቸውን አስተላልፈው፣ ለምስረታው መሳካት የሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማመስገን ጉባኤው ተጠናቋል። መረጃው የፈድሬሽኑ ፅሕፈት ቤት ነው።












