በሩሲያ ጥቃት በዩክሬን ዋና ከተማዋ ኪዬቭ ህይወታቸውን ያጡ ዩክሬናውያን ቁጥር ከ15 አለፈ።
በኪዬቭ የሰዎች ህይወት ከማለፉም ባሻገር 155ቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በጥቃቱ የተለያዩ የኪዬቭ አካባቢዎች መመታታቸው ይታወሳል። አዲስ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ሞስኮ በኪዬቭ ላይ የሚዔል እና ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት አድርሳለች።
የመኖሪያ ህንጻ በጥቃቱ መውደሙንም የኪዬቭ ባለስልጣናት አሳውቀዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአስር ቀናት ውስጥ ሩሲያ ተኩስ አቁም ላይ ካልደረሰች እርምጃ እንወስዳለን ባሉበት ሰዓት ነው ሞስኮ ከባድ ጥቃት እየሰነዘረች ያለው።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የመወያየት ፍላጎት እንደሌላቸውም አስታውሰዋል። ሩሲያ በዩክሬን የመከላከያ መሰረተ ልማት ላይ ትኩረት አድርጌ ጥቃት ሰነዘርኩ ብትልም ንጹሃንን ሰለባ አድርጋከች በሚል በኪዬቭ ትከሰሳለች።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












