የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእስራኤል ወደ ሀገራቸው የሚገቡ ምርቶች ላይ የ15 በመቶ ታክስ ጭማሪ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ምሽቱን ባፀደቁት አዲስ የንግድ ፖሊሲ እስራኤልን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ ማድረጋቸው ተሰምቷል። ጭማሪው ከመጪው ነሀሴ 7 አንስቶ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
ጭማሪውን ተከትሎ የእስራኤል የፉይናንስ ሚኒስትር ከሌሎች ሀገራት አንፃር የተጨመረብን አነስተኛ ነው፤ ይህም የሆነው ከትራምፕ ጋር በነበረን ጥሩ ውይይት ነው ብለዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












