አሜሪካ በተለያዩ ክፍሎች የጣለው ከባድ ዝናብና ያስከተለው ጎርፍ የድንገተኛ አደጋ ማስጠንቀቂያ እንድታወጅ ማስገደዱን ተነግሯል
በአሜሪካ ኒውዮርክ ሲቲና በኒውጀርሲ ግዛቶች የጣለው ሃይለኛ ዝናብና ያስከተለው ከባድ ጎርፍ ለአውሮፕላኖች በረራ ሳይቀር ችግር መፍጠሩና የድንገተኛ አደጋ ማስጠንቀቂያ እንዲታወጅ አድርጓል ነው የተባለው።
ትናንት አመሻሹን የጣለው ከባድ ዶፍ ዝናብ ነጎድጓዳማና ነፋስ አዘል ከመሆኑ የተነሳ በኒውዮርክ ሲቲ በዋሽንግተን ዲሲና በኒውዮርክ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከስቷል ነው የተባለው።
በዚያም የተነሳ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን የኢዲያ ቱደይ ዘገባ ያስረዳል።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












