የቀድሞው የአርሰናል አማካኝ ግራኒት ዣካ ከጀርመኑ ከለብ ባየር ሊቨርኩሰን በመልቀቅ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አዳጊውን ሰንደርላንድ ተቀላቅሏል።
በያዝነው የዝውውር መስኮት አሰልጣኙን ጨምሮ ቁልፍ ተጫዋቾቹን ያጣው ባየር ሊቨርኩሰን ዣካን ለማቆየት ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም። የ32 አመቱ አማካኝ በስታዲየም ኦፍ ላይት ለእስከ አውሮፓውያኑ 2028 የሚያቆየውን የ3 አመት ውል ፈርሟል።
በዝውውር ገበያው 9ኛ ተጫዋቹን ያስፈረመው ሰንደርላንድ ለስዊዘርላንዳዊው ተጫዋች 20 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ አድርጓል። ግራኒት ዣካ በ2023 ከመድፈኞቹ በመልቀቅ በባየር ሊቨርኩሰን የቡንደስ ሊጋ ዋንጫ አሸናፊ መሆን መቻሉ አይዘነጋም።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












